Saturday, December 21, 2019

የጃንሆይ ቮልስዋገን ዛሬ በቦሌ ትታያለች

አባትና ልጅ በቮልስነገ በቦሌ ጎዳና ቮልስዋገኖች ተግተልትለው ያልፋሉ፤ ከነሙሉ ክብርና ሞገሳቸው፡፡ በቁጥር 160 ይሆናሉ፡፡ ከነዚህ መካከል ቢያንስ አንዷ ታሪካዊ ናት፡፡ የጃንሆይ ቮልስ!
ለ46 ዓመታት ኢትዮጵያን ‹‹የሾፈሯት›› ጃንሆይ በመለዮ ለባሾቹ ከዙፋናቸው ሲገረሰሱ ከሞቀው ቤተ መንግሥት ‹‹ተሾፍረው›› የወጡት በዚች ቮልስዋገን ነበር፡፡
ያን ጊዜ ሾፌራቸው የነበሩት ጄኔራል ሉሉ እንግሪዳ ይባላሉ፡፡ እርሳቸው በሕይወት የሉም ዛሬ፡፡ ባለቤታቸው እማማ አጸደ ግን ቮልስዋገኗን ወርሰዋታል፡፡
ይቺ ቮልስ የታሪክ ድር እያደራች ዛሬም በአዲስ አበባ ጎዳናዎች ላይ ሽር ትላለች፡፡ ምናልባት በመኪና ቋንቋ ‹‹ቀሪን ገረመው›› እያለችን ይሆን?
ቮልስዋገኖች ተደርድረውImage copyrightVOLKSWAGEN ETHIOPIA, MICHEAL GET

ዝቅተኛ በሆነ ዋጋ የሚሸጥ፣ ማንም የአርያን ዘር ነኝ የሚል ኩሩ ጀርመናዊ ባልተጋነነ ዋጋ ሊገዛው የሚችል የደስተኛ ቤተሰብ መኪናን የሚወክል የተሽከርካሪ ፋብሪካ እንዲቆቋም አዘዘ፡፡
ይህን ቀጭን ትእዛዝ ተከትሎ አንድ በወቅቱ ግዙፍ ሊባል የሚችል የመኪና ማምረቻ ተቋቋመ።
ሆኖም ምርቱ በገፍ ከመጧጧፉ በፊት የ2ኛው የዓለም ጦርነት ተጀመረና ሁሉም ነገር ወደ ጦር ግንባር ተባለ። ቮልስ ሊያመርት የተባለው ፋብሪካም የጦር መሣሪያ ማምረት ያዘ።
የማያልፉት የለም ጦርነቱ ሂትለርን ይዞ አለፈ። የዓለም ጦርነቱ ሲያባራ በዓለም ዝነኛ ለመሆን እጣ ፈንታዋ የሆነች አንዲት መኪና ተመረተ
ለመኪናዋ ስያሜ ለመስጠት ብዙም ያልተቸገሩ የሚመስሉት አምራቾቿ ስሟን ቮልስዋገን አሏት። 'የሕዝብ መኪና' እንደማለት፡፡
ጢንዚዛ የመሰለችው ቮልስ መኪና ተወለደች። በምድር ላይ እንደርሷ በተወዳጅነት ስኬታማ ሆኖ የቆየ የመኪና ዘር የለም።
የአውቶሞቲቭ ተንታኞች ቮልስ ቢትልን ልዩ የሚያደርጋት በሀብታምና ሀብታም ባልሆነ ሕዝብ በእኩል መወደዷ ነው ይላሉ።
ምርቷ ሙሉ በሙሉ እስኪቆም ድረስ በጀርመን፣ በብራዚልና በሜክሲኮ 21 ሚሊዮን 529ሺህ፣ 464 ያህል ተመርተዋል። ስንት ሺዎቹ ወደኛ አገር እንደመጡ ግን በውል አይታወቅም።
"ቮልስዋገን ኢትዮጵያ" ማኅበር በሕግ ሲመሠረት አንዱ ሥራው የቆሙና በሕይወት ያሉ ቮልሶችን በትክክል መቁጠርና አባላትን መመዝገብ ይሆናል።

No comments:

Post a Comment