Saturday, December 21, 2019

የጃንሆይ ቮልስዋገን ዛሬ በቦሌ ትታያለች

አባትና ልጅ በቮልስነገ በቦሌ ጎዳና ቮልስዋገኖች ተግተልትለው ያልፋሉ፤ ከነሙሉ ክብርና ሞገሳቸው፡፡ በቁጥር 160 ይሆናሉ፡፡ ከነዚህ መካከል ቢያንስ አንዷ ታሪካዊ ናት፡፡ የጃንሆይ ቮልስ!
ለ46 ዓመታት ኢትዮጵያን ‹‹የሾፈሯት›› ጃንሆይ በመለዮ ለባሾቹ ከዙፋናቸው ሲገረሰሱ ከሞቀው ቤተ መንግሥት ‹‹ተሾፍረው›› የወጡት በዚች ቮልስዋገን ነበር፡፡
ያን ጊዜ ሾፌራቸው የነበሩት ጄኔራል ሉሉ እንግሪዳ ይባላሉ፡፡ እርሳቸው በሕይወት የሉም ዛሬ፡፡ ባለቤታቸው እማማ አጸደ ግን ቮልስዋገኗን ወርሰዋታል፡፡
ይቺ ቮልስ የታሪክ ድር እያደራች ዛሬም በአዲስ አበባ ጎዳናዎች ላይ ሽር ትላለች፡፡ ምናልባት በመኪና ቋንቋ ‹‹ቀሪን ገረመው›› እያለችን ይሆን?
ቮልስዋገኖች ተደርድረውImage copyrightVOLKSWAGEN ETHIOPIA, MICHEAL GET

ዝቅተኛ በሆነ ዋጋ የሚሸጥ፣ ማንም የአርያን ዘር ነኝ የሚል ኩሩ ጀርመናዊ ባልተጋነነ ዋጋ ሊገዛው የሚችል የደስተኛ ቤተሰብ መኪናን የሚወክል የተሽከርካሪ ፋብሪካ እንዲቆቋም አዘዘ፡፡
ይህን ቀጭን ትእዛዝ ተከትሎ አንድ በወቅቱ ግዙፍ ሊባል የሚችል የመኪና ማምረቻ ተቋቋመ።
ሆኖም ምርቱ በገፍ ከመጧጧፉ በፊት የ2ኛው የዓለም ጦርነት ተጀመረና ሁሉም ነገር ወደ ጦር ግንባር ተባለ። ቮልስ ሊያመርት የተባለው ፋብሪካም የጦር መሣሪያ ማምረት ያዘ።
የማያልፉት የለም ጦርነቱ ሂትለርን ይዞ አለፈ። የዓለም ጦርነቱ ሲያባራ በዓለም ዝነኛ ለመሆን እጣ ፈንታዋ የሆነች አንዲት መኪና ተመረተ
ለመኪናዋ ስያሜ ለመስጠት ብዙም ያልተቸገሩ የሚመስሉት አምራቾቿ ስሟን ቮልስዋገን አሏት። 'የሕዝብ መኪና' እንደማለት፡፡
ጢንዚዛ የመሰለችው ቮልስ መኪና ተወለደች። በምድር ላይ እንደርሷ በተወዳጅነት ስኬታማ ሆኖ የቆየ የመኪና ዘር የለም።
የአውቶሞቲቭ ተንታኞች ቮልስ ቢትልን ልዩ የሚያደርጋት በሀብታምና ሀብታም ባልሆነ ሕዝብ በእኩል መወደዷ ነው ይላሉ።
ምርቷ ሙሉ በሙሉ እስኪቆም ድረስ በጀርመን፣ በብራዚልና በሜክሲኮ 21 ሚሊዮን 529ሺህ፣ 464 ያህል ተመርተዋል። ስንት ሺዎቹ ወደኛ አገር እንደመጡ ግን በውል አይታወቅም።
"ቮልስዋገን ኢትዮጵያ" ማኅበር በሕግ ሲመሠረት አንዱ ሥራው የቆሙና በሕይወት ያሉ ቮልሶችን በትክክል መቁጠርና አባላትን መመዝገብ ይሆናል።

'ሜክሲኳዊ ስለሆነች' ብላ ታዳጊ የገጨችው አሜሪካዊት ታሠረች

ኒኮል ማሪሜክሲኳዊ" ትመስላለች ያለቻትን ታዳጊ ሆነ ብላ የገጨች አሜሪካዊት በግድያ ሙከራ በቁጥጥር ሥር ዋለች።
የ14 ዓመቷ ታዳጊ የተገጨችው ወደ ትምህርት ቤት እየሄደች ሳለ እንደነበር ፖሊስ ተናግሯል። ፖሊሶች ታዳጊዋ የተገጨችው ሆነ ተብሎ እንደሆነ እንደደረሱበት ባለፈው ማክሰኞ በሰጡት መግለጫ አስታውቀዋል።
የፖሊስ ኃላፊው ማይክል ቬኔማ እንደተናገሩት፤ ተጠርጣሪዋ ታዳጊዋን የገጨችው ሆነ ብላ እንደሆነ ስታምን በጣም ተደንቀዋል።
"ታዳጊዋን የገጨቻት ሜክሲኳዊ ስለሆነች እንደሆነ ለመርማሪዎች ተናግራለች። የሚያንቋሽሽ ነገርም ተናግራለች" ሲሉ ገልጸዋል።
ሰዎችን ለሚጠሉ፣ ጥቃት ለመሰንዘር ለሚነሳሱ ግለሰቦችም ማኅበረሰቡ ቦታ እንደሌላቸው ኃላፊው ተናግረዋል።
የ42 ዓመቷ አሜሪካዊት ታዳጊዋን በገጨቻት እለት በሌላ ወንጀል ተጠርጥራ ፖሊስ ጣቢያ ቆይታ ነበር። ፖሊሶች ተጠርጣሪዋ ላይ የጥላቻ ተግባር ክስ እንደሚመሰርቱ ገልጸዋል።

ሶማሊያዊያን የአንበጣውን መንጋ ለምግብነት በማዋል እየተዋጉት ነው

አንበጣ ለምግብነት ሲዘጋጅበሰሜናዊ የኢትዮጵያ ክፍል እንደተስተዋለው ሁሉ ጎረቤት ሃገር ሶማሊያም በ25 ዓመታት ውስጥ አይታ የማታውቀው ከፍተኛ የአንበጣ መንጋ ወረራ አጋጥሟታል።
በሃገራችን የአንበጣውን መንጋን ከፍተኛ ድምጽ በማውጣት ነበር ህዝቡ ከአካባቢው ሲያባረው የቆየው።
የጎረቤት ሃገር ሶማሊያ ዜጎች ግን መፍትሄ ያሉትን ሌላ መላ ዘይደዋል። ይህም፤ የአንበጣ መንጋውን መያዝ፣ በውሃ መዘፍዘፍ፣ አጠንፍፎ በዘይት ጠብሶ መመገብ።
በሶማሊያ አዳዶ ከተማ የሚገኙ ነዋሪዎች አንበጣን ጠብሰው ከሩዝ እና ከፓስታ ጋር ለምግብነት እያዋሉት ነው።
አንዱ የከተማዋ ነዋሪ "አንበጣው ከአሳ በላይ ልዩ ጣዕም አለው" ያለ ሲሆን ሌላኛው ደግሞ የአንበጣው የንጥረ ነገር ይዘት ፍቱን የሆነ መድሃኒት እንደያዘ እንደሚያምን ይናገራል።
ይሄው ግለሰብ ዩኒቨርሳል ሶማሊያ ለተሰኘ የቴሌቪዥን ጣቢያ አስተያየቱን ሲሰጥ፤ አንበጣው ውስጥ የሚገኘው ንጥረ ነገር የደም ግፊቱን እንደሚያስተካክልለት እና የጀርባ ህመሙን እንደሚያሽልለት ተስፋ አድርጓል።

ኢትዮጵያ ሳተላይት ማምጠቋ ለምን ይጠቅማታል?

ሳተላይቷ ከቻይና ስትመጥቅ







ኢትዮጵያ በታሪኳ የመጀመሪያ የሆነችውን ሳተላይት ከቻይና የሳተላይት ማስወንጨፊያ ጣቢያ ወደ ህዋ ላከች።

ሳተላይቷ ለግብርና፣ ለማዕድን፣ ለአካባቢ ጥበቃ፣ ለአየር ንብረት ጥበቃና ለመልከዓ ምድር ጥናት የመረጃ አገልግሎትን ትሰጣለች ተብሏል።

Ethiopian Remote Sensing Satellite - 01 (ETRSS - 01) የተሰኘችው ሳተላይት በቻይና መንግስት የተገነባች ሲሆን በግንባታው ሂደትም በርካታ ኢትዮጵያውያን ባለሞያዎች ከቻይና አጋሮቻቸው ጎን ተሰልፈው ከፍተኛ አስተዋጽኦ አበርክተዋል፡፡

ከቻይና 6 ሚሊየን ዶላር ተለግሶ የተሠራችው ይህቺ ሳተላይት በአጠቃላይ 210 ሚሊየን እንደፈጀች ተነግሯል።

• ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ሊያድኑት የነበረው ለገሰ ወጊ ማን ነበሩ?

የሳተላይቷ የመረጃ መቀበያ እንጦጦ ላይ የተሠራ ሲሆን ከማምጠቅ ሥራው ጀምሮ ቁጥጥሩ ሙሉ ለሙሉ እንጦጦ ላይ በኢትዮጵያውያን የህዋ ዘርፍ ባለሞያዎች ይከናወናል።

ይህ ሳተላየት የማምጠቅ ሥራ ከተለያዩ አካላት 10 ሚሊየን ዶላር የገንዘብ ድጋፍ ማግኘቱ የተነገረ ሲሆን የኢትዮጵያ መንግሥትም ተጨማሪ በጀት መመደቡ ተገልጿል።

ቻይናውያን ኢንጂነሮች ኢትጵያውያንን እያሰለጠኑ ሳተላይቱ ቻይና ውስጥ እንዲሁም በከፊል ኢትዮጵያ ውስጥ ተገነብቷል።

70 ኪሎ ግራም የሚመዝነው ሳተላይት ታኅሣሥ 10፣ 2012 ዓ. ም. ማለዳ ከቻይና መምጠቁ በቀጥታ በተላለፈ ፕሮግራም ታይቷል።

ሳተላይቱ በቻይና እገዛ ከምድረ ቻይና ይምጠቅ እንጂ፤ "ተቆጣጣሪዋም፣ አዛዧም ኢትዮጵያ ናት" ይላሉ የኢትዮጵያ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ሰለሞን በላይ ለቢቢሲ።

ሳተላይት ማምጠቅ ለምን አስፈለገ?
የህዋ ጥናት በዓለም ላይ በፍጥነት እየዘመኑ ካሉ ዘርፎች መካከል ይጠቀሳል። የሰው ልጅ ምድር ጠባው አልያም ከምንኖርበት ዓለም ውጪ ያለውን ለማወቅ ጓጉቶ ዘወትር እየቆፈረ ነው።

ከህዋ ፍተሻ በተጨማሪ ህዋን ተጠቅሞ መሬትን ማሰስ የመሬት ምልከታ ሳተላይት ተግባር ነው። ሳተላይቱ መረጃ ሲሰበስብ ይህ ቀረህ አይባለውም። ከግዙፍ ክንውኖች እስከ ጥቃቅን እንቅስቃሴዎች ይመዘግባል።

እንደ ባለሙያዎች አባባል ሳተላይቱ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ አለው። የአየር ንብረት ለውጥን ለመቆጣጠር፣ የተፈጥሮ አደጋዎች ከመድረሳቸው አስቀድሞ ለመተንበይ፣ ደህንነትን ለመጠበቅ ወዘተርፈ ይውላል።

በእርግጥ ብዙዎች በታዳጊ ሀገር የህዋ ጥናት አስፈላጊነቱ ላይ ጥያቄ ቢያነሱም፤ ዶ/ር ሰለሞን "ህዋ እንደ ኢትዮጵያ ላሉ ሀገሮች የመኖርና ያለመኖር ጥያቄ ነው፤ ቅንጦት አይደለም" ይላሉ።

የአየር ንብረት ለውጥ የመላው ዓለም ስጋት በሆነበት ዘመን፤ አንዳች ተፈጥሯዊ አደጋ ከመድረሱ በፊት አስቀድሞ መረጃ ማግኘት ብልህነት ነው።

የዛፍ ቁጥር፣ የአየር ንብረት ለውጥና ሌሎችም መረጃዎች ከተሰበቡ በኋላ እንደ ጎርፍ ያሉ አደጋዎች ከመከሰታቸው በፊት መተንበይ ይቻላል።

• በቤታችን ውስጥ ያለ አየር የጤናችን ጠንቅ እንዳይሆን ማድረግ ያለብን ነገሮች

ግብርና ቀዳሚ መተዳደሪያ በሆነባት ሀገር የቱ አካባቢ ምርታማ ነው? የአየር ንብረት ለውጥ ይኖር ይሆን? የሚሉ ጥያቄዎች በቀላሉ እንዲመለሱ የሳተላይቱ መረጃ አስፈላጊ ይሆናል።

ዶ/ር ሰለሞን እንደሚሉት፤ አንድ የግብርና አካባቢን የሚያሳይ ፎቶግራፍ ስለ እርሻ መሬቱ፣ ስለ ውሀው፣ ስለ አፈሩ ዝርዘር መረጃ ይሰጣል። መረጃዎቹን በመጠቀም ምርታማ የሆኑ አካባቢዎችን መለየት፣ የምርት መጠንን በትክክል ማወቅም ይቻላል።

ኢንዱስትሪዎች እየተስፋፉ በመጡባት ኢትዮጵያ፤ ፋብሪካዎች የት መገንባት አለባቸው? ለሚለው ጥያቄ የሳተላይቱ መረጃ መልስ ሊሰጥ ይችላል።

ሕዝብ መቁጠር ሲያስፈልግ ከዘልማዳዊው መንገድ ሳተላይቱን መጠቀም ይመረጣል። ትክክለኛ መረጃ ከማግኘት፣ ገንዘብና የሰው ሀይል ከማዳን አንጻርም የተሻለው አማራጭ ነው።

Image copyrightZACHARIAS ABUBEKER
ሳተላይቱን ደህንነትን ከመጠበቅ ጋር የሚያስተሳስሩት ባለሙያዎች አሉ።

ዶ/ር ሰለሞን በበኩላቸው "በመርህ ደረጃ ህዋ የሚውለው ለሰላማዊ እንቅስቃሴ ነው" ብለው፤ ለጦርነት፣ ለጦር መሳሪያ ማሳለጫነት እንደማይውል ያስረዳሉ።

የ'ኢንተርናሽናል የአውተር ስፔስ' ተቋም አባል መሆን፤ ኢትዮጵያን ከመሰል ድርጊቶች እንደሚያግዳትም አክለዋል።

ኢትዮጵያ እስካሁን መረጃውን እንዴት ታገኝ ነበር?
ኢትዮጵያ እነዚህን መረጃዎች ሳተላይት አምጥቀው ፎቶ ከሚያስነሱ ሀገሮች ትሸምት ነበር። ዶ/ር ሰለሞን የሚያጣቅሱት ከአምስት ዓመት በፊት በተሰራ ጥናት መሰረት ኢትዮጵያ የሳተላይት መረጃን ለመግዛት በዓመት 250 ሚሊየን ብር ታወጣለች።

ጥናቱ ለደህንነት የሚወጣውንና ዩኒቨርስቲዎች የሚከፍሉትን አያካትትም። ወጪው ከዓመት ወደ ዓመት እንደሚጨምርም ያስረዳሉ።

የከተሞች መስፋፋት፣ ኢንቨስትመንቶች እየጨመሩ ሲሄዱም በዛው መጠን የመረጃው አስፈላጊነት ይንራል። የሚወጣው ገንዘብም እንዲሁ። ሳተላይት ማምጠቅ እነዚህን ወጪዎች እንደሚቀንስ ይጠበቃል።

አፍሪካ ውስጥ መሰል ሳተላይት ለሌላቸው ሀገሮች መረጃ መሸጥም ይቻላል። የኢትዮጵያ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተሩ "ትልቅ ቢዝነስ ነው" የሚሉትም ለዚሁ ነው።

Image copyrightZACHARIAS ABUBEKER
"ሲያስፈልግ መረጃ እንሸጣለን። ከኛ የላቀ ቴክኖሎጂ ካላቸው ሀገሮች ጋር መረጃ መለዋወጥም ይቻላል፤"

ኢትዮጵያ በህዋ ጥናት የት ደረሰች?
ዓለም በህዋ ጥናት ቴክኖሎጂ እየመጠቀ ሄዷል። ኢትዮጵያ ከተቀረው ዓለም አንጻር ጀማሪ ናት። አፍሪካ ውስጥ ናይጄሪያ፣ ደቡብ አፍሪካ፣ አልጄሪያና ግብጽ ጥሩ ስም አላቸው።

ኢትዮጵያ "ህዋ ለልማት" የሚል የምሥራቅ አፍሪካ ሀገሮች ትብብር ቢሮ አቋቁማ አበረታች እንቅስቃሴ ማድረጓ ተጠቃሽ ስኬት ነው።

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በ2030 ይደረስባቸዋል ብሎ ካስቀመጣው ግቦች አብዛኞቹ የህዋ ቴክኖሎጂን ያማከሉ መሆናቸው፤ ዘርፉን ችላ ማለት እንደማያዋጣ ያመላክታል።

ዶ/ር ሰለሞን የመሬት ምልከታ ሳተላይት ማምጠቅ ኢትዮጵያ በህዋ ሳይንስ ዘርፍ እንቅስቃሴ እያደረገች ስለመሆኑ ለዓለም መልእክት ማስተላለፊያ መንገድ እንደሚሆን ያምናሉ።

• ኢትዮጵያ ሳተላይት ማምጠቅ ለምን አስፈለጋት?

"ቴክኖሎጂው እጅግ አስፈላጊ ነው፤ ሳተላይቱን ማምጠቅ ኢትዮጵያን በህዋ ዘርፍ ጠንካራ ተወዳዳሪና እኩል ተጽእኖ ፈጣሪ ማድረግ የሚያስችል ነው"

ሳተላይቱ አንዴ ከመጠቀ በኋላ ከሶስት እስከ አራት ዓመት ያገለግላል። ከዛ በላይ ሊቆይም ይችላል። በዓለም አቀፍ ሕግ መሰረት፤ የመሬት ምልከታ ሳተላይቶች ህዋ ላይ እንዲቆዩ የሚፈቀደው ለስምንት ዓመት ነው።

ኢትዮጵያ ከምታመጥቀው ሳተላይት፤ በየአራት ቀኑ የመላው ኢትዮጵያ መረጃ የዓለም ደግሞ በ55 ቀን ይገኛል።

በህዋ ምርምር ዘርፍ ቅርብ ጊዜ እውን ይሆናሉ ተብለው ከሚጠበቁ ፕሮጀክቶች ውስጥ ላሊበላ ላይ ይገነባል የተባለው ዓለም አቀፍ ኦፕቲክ ቴሌስኮፕ አንዱ ነው።