በተለያዩ የአገሪቷ ክፍሎች በሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች በሚከሰቱ
ግጭቶች የሰዎች ሕይወት አልፏል፣ የአካል ጉዳት አጋጥሟል፣ በንብረት ላይም ጉዳት ደርሷል። ከእነዚህም
ዩኒቨርሲቲዎች አንዱ ጎንደር ዩኒቨርሲቲ ነበር።
ዩኒቨርሲቲው ችግሮቹን ለመፍታት "አንድ ተማሪ ለአንድ ቤተሰብ" የሚለውን ጨምሮ የተለያዩ መፍትሄ ይሆናሉ ያላቸውን ተግባራዊ እያደረገ ይገኛል። በዚህም ታህሳስ 22/2012 ዓ.ም የዩኒቨርሲቲው ሴኔት ባካሄደው አስቸኳይ ስብሰባ፤ በግጭቶቹ በተለያየ ደረጃ ተሳትፈዋል ባላቸው ተማሪዎች፣ መምህራን፣ የአስተዳደር ሠራተኞችና የጤና ባለሙያ ላይ እርምጃ መወሰዱን የዩኒቨርሲቲው ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክተር ይዳኝ ማንደፍሮ ለቢቢሲ ገልፀዋል።
እርምጃው የተወሰደው ከኅዳር 4 ጀምሮ በዩኒቨርሲቲው ከተፈጠሩ ግጭቶች ጋር በተያያዘ ነው።
No comments:
Post a Comment